ልዩ ፀጋ Liyu Tsega

ግላዊነት

ረቂቅ — የሕግ ባለሙያ ከመገምገሙ በፊት የመጨረሻ አይደለም።

ስሪት፦ 2026-11-21

ምን እንሰበስባለን

አካውንት ሲከፍቱ ስምዎን እና ስልክ ቁጥርዎን እንይዛለን፤ የይለፍ ቃልዎ ተመልሶ ሊነበብ በማይችል መልክ (scrypt hash) ብቻ ይቀመጣል። ክፍያ ሲፈጽሙ የክፍያ መዝገብ ይቀመጣል። በFamily የሚለጥፉት በFamily ላይ ይቀመጣል።

ትዝታዎችዎ የት ይቀመጣሉ

ዲያሪ፣ ፎቶ፣ ድምፅ እና ደብዳቤዎች በስልክዎ ይቀመጣሉ። ሲገቡ ቅጂያቸው በእያንዳንዷ እናት የራሷ ቁልፍ (AES-256-GCM) ተመስጥሮ በሰርቨራችን ይቀመጣል። አናሳትማቸውም፤ ለማስታወቂያም አንጠቀምባቸውም።

የሚጋሩት

በFamily የሚለጥፏቸው ልጥፎች ለFamily አባላት ይታያሉ፤ መገለጫዎን፣ ታሪኮችዎን (stories)፣ አስተያየትና መልእክት ማን እንደሚያይ ወይም እንደሚልክ በግላዊነት ቅንብር ይወስናሉ። «ልዩ ስጦታ» ሲያዝዙ የላኩት ፎቶ ለዝግጅቱ ብቻ ይውላል፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ (አሁን 30 ቀን) በራሱ ይሰረዛል።

መከታተያ የለም

የማስታወቂያ ወይም የመከታተያ (analytics) ስክሪፕት አንጠቀምም።

ፈቃድ (consent)

ሲመዘገቡ የአገልግሎት ውሎቹን እንደተቀበሉ እና ይህን መመሪያ እንዳነበቡ ራስዎ ምልክት ያደርጋሉ፤ የተቀበሉት ስሪት እና ሰዓቱ ይመዘገባል። ስለ አዳዲስ ነገሮች መልዕክት መቀበል የተለየ እና አማራጭ ምርጫ ነው፤ እርስዎ ካልመረጡት አይበራም።

ማጥፋት

በSettings → «የእርስዎ መረጃ» → «ሁሉንም ይሰርዙ» ትዝታዎች ከስልክዎ እና ከባክአፑ ይጠፋሉ።

መለያ ማጥፋት

በMy account → «መለያዬን አጥፋ» የይለፍ ቃልዎን አስገብተው መለያዎን ማጥፋት ይችላሉ። ስምዎ፣ ስልክ ቁጥርዎ፣ ፎቶዎ፣ በFamily ያሉ ልጥፎችዎ፣ አስተያየቶችዎ፣ ታሪኮችዎ እና መልዕክቶችዎ፣ በሰርቨሩ ያለው ባክአፕ፣ ስጦታዎች እና የግብዣ ገጾች ወዲያውኑ ይጠፋሉ፤ የወል ሊንኮቻቸውም መስራት ያቆማሉ። የተከፈለ ገንዘብ መዝገብ ብቻ ያለ ስም እና ስልክ ይቀመጣል፤ የሚቀመጥበት ጊዜ በሕግ የሚወሰን ነው። በሰርቨሩ የዕለት ዳታቤዝ ባክአፖች ውስጥ ያሉ ቅጂዎች ባክአፖቹ በሚሰረዙበት ጊዜ (በ14 ቀናት ውስጥ) ይጠፋሉ። Wallet ውስጥ ገንዘብ ወይም ያልተጠናቀቀ ክፍያ/ትዕዛዝ ካለ መጀመሪያ እንዲጨርሱት እንጠይቃለን።

ያግኙን

ጥያቄ ካለዎት በTelegram @pixeldigitalempirebot ወይም በአፑ ውስጥ ባለው «እገዛ» ያግኙን።

ናሙናዎቹን በነፃ ይመልከቱልዩ ፀጋን ክፈት